Song Lyrics

ያው ነው

ዛሬ ብዬ የጠራሁት ቀን ትላንት ተብሎ አልፎ ሲወራ ብርቱ መስሎ የታየው ሰው ለቀብሩ ሞቱ ሲሰማ ፍጥረት ቦታውን ለቆ የቆመው ደግሞ ወድቆ ቀና ስል ኢየሱስ ያው ነው ቀና ስል ጌታዬ ያው ነው ነው ይባላ ቀና ይባላ ቀና ብርቱ የሆነ አምላክ አለና ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ አለሁ አለሁ ያለው ሰው ድንገት ጉልበት ሲከዳው ሁሉን ዘመን በቃ ሲለው እንደ ጥላ ሲያሳልፈው ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ኢየሱስ ዛሬም ያው ግርማዊነቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ነገም ያው ይባላ ቀና ይባላ ቀና ብርቱ የሆነ አምላክ አለና ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ አደራ የተባለው ለአደራው ሳይበቃ ዓይን የተጣለበት ከስፍራው ሲታጣ ማነው ጽኑ ብዬ ስጠይቅ ጥያቄ ቃሉ እንዲህ እያለ ፈሰሰ ከውስጤ ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም እስከ ለዘላለም ያው ነው አንቱ ተብሎ ሚወራለት ጐንበስ ቀና ሚባልለት እንዲያው ሲቀር በትዝታ አንደ እለ ግን ሕያው ጌታ ፡ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ኢየሱስ ዛሬም ያው ግርማዊነቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ነገም ያው ይባላ ቀና ይባላ ቀና ብርቱ የሆነ አምላክ አለና ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection