እግዚአብሔር ሆይ እንዳንተ ያለ ማንም የለም ( 2x) አዝ፦ አንተ ታላቅ ነህ የሥምህ ሥልጣን ታላቅ ነው (፬x) ከጣዖታት ዘንድ ፊቴን አዙሬ ለአንተ ክብር ሆነልኝ መዝሙሬ ስል አንተ እና ሥምህ ታላቅ ነው ሌላ ቃላት መግላጫ ባጣ ነው ( 2x) አዝ፦ አንተ ታላቅ ነህ የሥምህ ሥልጣን ታላቅ ነው (፬x) ቢሰለፉ አማልክት በተርታ ካንዳቸውም መሳይ የለ ጌታ እንደ ስምህ: ነህ የሁሉ ገዢ ዘመንህ ዕድሜ አይባልም ከዚህ ልክ የለህም ወሰን የለህም ልክ የለህም መጠን የለህም በሰው ቋንቋ ከቶ አልገልጥህም ( 2x) ሥምህ ትልቅ ነው ለጠራው ሁሉ ሚሆን መዳኛ ሥምህ ትልቅ ነው ለደካከመው ብርታት ማግኛ አንተ ትልቅ ነህ በምንም ነገር ከቶ አትለካም አንተ ትልቅ ነህ ዘመን አያልቅም የለብህ ድካም