እንኮን ልመካ እንዲህ ነኝ ብዬ እኔ የእኔ ልል ቃል አስረዝሜ ኔን አስጀምሮ የሚያስጨርሰኜ ከራሴ ምለው አንዳችም የለም አሁን የሆንኩትን መሆን የመቻሌ ጌታ በአንተ እኮነው አይደለም በእኔ ክብር ሁሉ ለአንተይሁን # ፬ እኔ ለማለት __ቢሉልኝ ሰዎች ብጠራ ፡ ማንም አይገኝ በአሸዋ ላይ ቤቴን ስሥራ ፡ እርሱ ነው ስል ግን ተሰብሰቡና አዎ በሉልኝ ይህን ላረገው ታማኙ ጌታ (ክብር አምጡልኝ) # ፰ ስሙኝ ወገኖች ይህን ስናገር ብሕይወቴ ላይ ለሆነው ነገር እንኳን ልታበይ እኔን ላበዛ ትንፋሽ መንገዱን ከፍሎ እንደገዛ ከቶ አልመካም እንዲያው በከንቱ ከእኔ ሳይሆን ሁሉ ነው በእርሱ እ የሚለውን ፊደል ጀምሬ ን ለመጨረስ ኃይል የለኝ እኔ እያሉኝ ነው በአንተነው ጌታ ሁሉን አድርገህ የምታስመካኝ ሁንከኝ አለኝታ ክብር ሁሉ ለአንተይሁን # ፬ ኧረ ምንድ ነው ከእኔ ነው የምለው ኃይሌ ብርታቴ እጄ ያረገው ማበዛላቸው ብዙ እኔዎች ሁኑ ምላቸው በእኔ ክንዶች ምንም የለኝም የሚያስብለኝ እኔ ክብር ሚገባው ለአንተ ጌታዬ እንኮን ልመካ እንዲህ ነኝ ብዬ እኔ የእኔ ልል ቃል አስረዝሜ ኔን አስጀምሮ የሚያስጨርሰኜ ከራሴ ምለው አንዳችም የለም ክብር ሁሉ ለአንተይሁን # ፬