Song Lyrics

ዘላለማዊ

የማታረጀው ማትቀደደው ሀሩር ሲመጣ ማትቀየረው ዘላለማዊው ልብሴ የኔነቴ: ውበት:ግርማ ኢየሱስ ጌታዬ ነህ የክብር ሁሉ መደምደሚያ ዘላለማዊ ልብሴ ነህ ውበቴ [2X] አንተን ለብሶ ተጐናፅፎ እራቁቱን ማንስ ቀርቶ የለበሰህ ከበረ እንጂ መቼ ቆመ ውርደት ደጅ አንተን ያለ የታደለ እራቆቱ ተሸፈነ [2X] ዘላለማዊ ልብሴ ነህ ውበቴ [2X] ከአንተ ውጭ ሚለበስ ሁሉ የማያዛልቅ ቅጠል መሆኑ የተረዳ ሰው ሌላውን አውልቆ አንተን ሲለብሰህ አዳኙን አውቆ የሞትን ነፋስ ብርድን አይፈራ የዘላለሙን ለብሶሃልና [2X] ዘላለማዊ ልብሴ ነህ ውበቴ [2X] የማታረጀው ማትቀደደው ሀሩር ሲመጣ ማትቀየረው ዘላለማዊው ልብሴ የኔነቴ: ውበት ግርማ ኢየሱስ ጌታዬ ነህ የክብር ሁሉ መደምደሚያ ዘላለማዊ ልብሴ ነህ ውበቴ [2X]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection