Song Lyrics

ድንቅ ነህ

ጌታ ፈጣሪዬ ስለ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ስለ አካል ክፍሌ ላመሰግንህ እፈልጋለው ግሩም ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለው [ 2x] ግሩም ነህ የሰራሀኝ ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [ 2x] የማመስገኛ ምክንያት ከሆነ ከቁጥር በላይ እኔ ጋር አለ እግሬ ሲራመድ ሚዛን ጠብቆ ዓይኔም ሲያይልኝ ቅርብም አርቆ በራስ ቅሌ ላይ ሲበቅል ፀጉሬ ጣቶቼ ላይ ሲያድግ ጥፍሬ ውበት አላቸው በየቦታቸው ጌታዬ አንተ ነህ የሰራሃቸው [ 2x] ግሩም ነህ የሰራሀኝ ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [ 2x] ሰው ሰውን ቢሰራው ቢያበጀው እስትንፋስ ቢሰጠው የሚከፍለው አጥቶ ሁሉም ሰው መኖር በተሳነው ይተመን ቢባል በዋጋ የአካል ክፍሌ በዓለም ያለው ሃብት በሙሉ አይመጥን ለኔ እንዃን ሁሉንም ይቅርና አንዱንስ እንኳ መፍጠር ያልቻለው የሰው ልጅ እንዴት ይመካ ግሩም ነህ የሰራሀኝ ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [ 2x] በሚጥም ዜማ የሚያዜመው የአንተን ዝማሬ ገንዘብ ሊገዛው አይችል ይህ አንደበቴ [ 2x] ጌታ ፈጣሪዬ ስለ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ስለ አካል ክፍሌ ላመሰግንህ እፈልጋለው ግሩም ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለው [ 2x] ግሩም ነህ የሰራሀኝ ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [ 2x]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection