ሰው ከሆነበት አስደንጋጭ ወሬ ወየው ከሚያሰኝ ከክፉ ፍሬን አሄ ሳልርበተበት ሳልል የት ልግባ ከዓይኔ ሳይወጣ የሃዘን እንባ አዝ፦ ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (2x) ነፍሴ ማን አለና የቱን ለማን ስትል ድንገት ስታጣቸው ቃል የገቡላትን እጆቹን ዘርግቶ አቅፎ የተቀበላት በጣም በጭንቋ ቀን አላት የሚቤዣት (2x) አዝ፦ ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (2x) እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ የሚያድነኝ ገብቷል በሰፈሬ ለኃጢአተኛው የሚመጣው ዱላ የጻድቁን ቤት አይነካምና የመንፈሱን ቤት አይነካምና እሩትን ከተቤዣት ከቡሄዝ በልጦ ለተሻለው ኪዳን ለእኔ ዋስ የሆነው ልቤን የጣልኩበት ጌታ በጭንቄ ደራሽ ነው ሚያስመካ (2x) እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ የሚያድነኝ ገብቷል በሰፈሬ ለኃጢአተኛው የሚመጣው ዱላ የጻድቁን ቤት አይነካምና የመንፈሱን ቤት አይነካምና አዝ፦ ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (2x)