በሰማይ ፍቅር ልቡ ተውጦ የጽድቅን መንገድ ሊሄድ አቋርጦ የሥጋን ለባሽ ደጅ የጠላ ዛሬም ይኖራል ሆኖ ጥገኛ ያ ሰው ያ ሰው ፊቱን ብፈልግ ደጁን ብጠና ኧረ አትዘን ብሎ ያረገኝ ቀና ዛሬም የሚጥኝ እርሱን እላለሁ የእኔስ ደጋፊ ጌታ እግዚአብሔር ነው ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ የሚለው ተረት መች ይገባኛል ኢየሱስ ካለኝ ሁሉም እንዳለኝ መንፈስ ነግሮኛል በሰው የወጣ በሰው ይወርዳል የተሰጠውም በመንገድ ያልቃል የእኔ ኢየሱስ ግን በምድረ በዳ ምንጭን ያፈልቃል (ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ (ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ (ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ በልምምጥ ቃል በ??? ቋንቋ ተቀለጣጥፎ ሰው የተጠጋ ፍጻሜ ሳይደርስ አንገቱን ደፍቶ ቆሟል እዛጋ የአምላኩን ፊት እየፈለገ ጌታን በመፍራት ተግቶ የኖረ ላይቆም ይሄዳል የጌታን ማዳን እየሰበከ ዘንድሮ ሆኗል ምላስ ላላቸው የሰው ደጋፊ ለበዛላቸው ብለው ለሚሉ ጊታ ልኮኛል እንዲህ እንድላቸው እነ ኤሊያስ ሰልፍ እንደያዙ እኔን በቀባኝ ብለው ሲጓጉ ጌታ የደገፈው ዳዊት ተቀባ እነሱ እያዩ (ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ (ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ (ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ በሥጋ ለባሽ ዓይኑን የጣለ አለኝ እከሌ ለሁሉ ያለ የተመካበት ድንገት ሲሰበር ዓይኔ ይሄን አየ ከዘመድ አዝማድ ዓይኑን ያነሳ በአምላኩ ታምኑ ከዑር የወጣ አንዱን ደጋፊ አብርሃም ይዞ ከቶ ምን አጣ (ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ (ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ (ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ