አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ ( 2x) አትደግ ብሎ ትላንት የረገመኝ ጉድ ትሆናለህ ታያለህ እኮ ያለኝ የርግማን ትንቢቱ ይፍረስ በጌታ ሥም ልቤማ ደንግጦ ለርሱ እጅ አልሰጥም አዝ፦ በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ ( 2x) ከዘር ማንዘሮቼ ተወራርሶ የመጣ ነፃነት ከልክሎ መንገዴን የዘጋ ዛሬ በየሱስ ስም ጉልበቱ ይመታ ወዳጄ ብቻ ነው በቤቴ ላይ ጌታ አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ ( 2x) ውድቀቱን ለሚሹ ለሚመትቱበት ፡ በረከቱን ይዘው ሞት ለሚመኙለት ፡ ከሰማይ የሆነ ትንቢትን ይዣለሁ ፡ ለፃድቁ መልካም ይሆናል እላለሁ ፡ አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ አዝ፦ በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ ( 2x) ለቅዱሳን ሁሉ ክፉ የመደማችሁ ሥም እየጠራችሁ እርገሙ ብሏቸው የተናገሩት ቃል ይሁን ለራሳቸው ያጠመዱት ወጥመድ ዞሮ ይያዛቸው አዝ፦ በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፬x)