በግብፅ የነበረውን የህዝቡን ጩኸት የሰማ ጌታ ጊዜና ዘመን ጠብቆ ወደኔ መጣ በቃ አለው ( 2x) ያን ክፉ በቃ አለው ያን ክፉ ጌታዬ ከልሎኝ በክንፉ (፬x) ያቤቱታ ድምፄ ወደ ጆሮው ደርሶ የምህረት ፊቱን ወደኔ መልሶ ከጨቋኙ ገዢ ነፍሴን አላቋታል ውስጤን በደስታ እንዲህ አስብሎታል አሄ አስባለሁ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ ( 2x) እላለሁ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ ( 2x) በውርደቴ መንደር ክብር ያየሁበት የቆሰለው ልቤ የተፈወሰበት ( 2x) እላለሁ እላለሁ እንደ እግዚአብሔር የለም አሜን ( 2x) እንደ ወትሮው ሰላም አውለኝ ብዬ ስነሳ የፈሮኦንን ጡብ ልሰራለት ከቤት ስወጣ ያስገባሪዬን ገመድ ከላዬ ሊፈታልኝ አምላኬ መጣ ያዘንኩበትን ቀን ቀጥሮልኝ ግብፅን ለቅቄ ያን ቀን ስወጣ ፈርኦን ሲያየኝ እንዲህ አልኩታ ጉልበቴ ( 2x) ላዳነኝ ጌታ ነው ጉልበቴ አትበላው ከሳሼ በግብፅ የነበረውን የህዝቡን ጩኸት የሰማ ጌታ ጊዜና ዘመን ጠብቆ ወደኔ መጣ በቃ አለው ( 2x) ያን ክፉ በቃ አለው ያን ክፉ ጌታዬ ከልሎኝ በክንፉ (፬x)