Song Lyrics

አልነካም

ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ አዝ፦ አልነካም አልነካም በጠላቴ ላልነካ ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም ( 2x) ከአቤል ደም ይልቅ የሚናገር ደሙ እስከዛሬ ድረስ ትኩስ በመሆኑ የወረወርው ቀስት ፈልጎ አጥቶኛል የኢየሱሴ ደም በሙላት ጋርዶኛል ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም ( 2x) ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም ( 2x) ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ አዝ፦ አልነካም አልነካም በጠላቴ ላልነካ ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም ( 2x) ክፉ እንዲደሰት እንዲስቅ በእኔ ደግሶ እንዲበላ አይፈቅድም መድህኔ የቀባውን ሊያድን ይወጣል በግርማ አድኖኝ ስላየሁ እላለሁኝ ዘና ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም ( 2x) ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም ( 2x) ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ አዝ፦ አልነካም አልነካም በጠላቴ ላልነካ ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም ( 2x) ምክር ተመክሮብኝ መልክተኞች መጡ በክፉ ሴራቸው ህይወቴን ሊያጠምዱ ሰፈሬ ሲደርሱ አልቻሉም ሊቀርቡኝ በኢየሱሴ ደም ተሸፍኜ አዩኝ ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም ( 2x) ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም ( 2x) አዝ፦ አልነካም አልነካም በጠላቴ ላልነካ ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection