Song Lyrics

ባሰብኝ

የአምላኩን ምሥጋና ካፉ እወስዳለሁ በማመስገን ፈንታ ማጉረምረም እሞላለሁ ያለው ከሳሼ ሳይሆንለት ቀርቶ መላው ማንነቴ በደስታ ተሞልቶ ባሰብኝ ምን ትሆን ጠላቴ ባሰብኝ ይመስገን አምላኬ ( 2x) ሳላይ የሚያይልኝ ሳልሰማ ሚሰማ ብጠራው ሚያደምጠኝ አምላክ አለኝና አለቴ ውስጥ ሆኜ ወደ ውጭ እያየሁ በሚፈልገኝ ላይ እስቅበታለሁ አዝ፦ አለኝ እና ጠባቂ የማያልፈው ክፉ አጥቂ አለኝ እና ጠባቂ ( 2x) እልፍ ከሆኑት የጠላቴ እርግማኖች መልካም ካልሆኑት አሰናካይ ንግግሮች አንዲቱ ያምላኬ ምርቃት ከሱ እርግማን ትልቃለች እስከ ሺህ ትውልድ በበረከት ታኖራለች ይቀመጥ እንጂ ጠላቴ ሸንጎ በመንገዴ ላይ ወጥመድ አድርጎ ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ አለኝ ዋስትና አልሰጋም እኔ አዝ፦ አለኝ እና ጠባቂ የማያልፈው ክፉ አጥቂ አለኝ እና ጠባቂ ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection