Song Lyrics

እጁ መጣ

ቀን ተቀጥሮ ለመሞቴ ሊያበቃ ይህ ታሪኬ ጀንበር ልትጠልቅ አዘቅዝቃ ያለኝ ተስፋ ሊያበቃ ሲል እጁ መጣ (፬x) ጌታ መጣ (፬x) እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x) ለብዙ ለብዙ ዘመናት ጦር ከጁ ያልተለየው ወርውሮ ወርውሮ የማይስተው ሳኦል የተባለው ዳዊት ላይ ወርውሮ ለምንድነው የሳተው አዝኖለት አይደለም እግዚአብሔር ጋርዶት ነው ( 2x) የዚህ አለም ገዢ በጥልቅ ተቀምጦ ሲፎክር አየሁት የእኔ አይኔ ተከፍቶ ሲፎክር ሰምቼ ልቤ ሲርድብኝ ጌታ መንፈስ ቅዱስ እኔን ተናገረኝ የፉከራ ድምፁን ሰምተህ ከምትፈራ የተፃፈለትን ሂድ እና አንብበው ቅዱሱን መጽሐፍ ገልጬ ሳነበው የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል ነው እሚለው እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x) የጠላቴ ውጥኑ እቅዱ ተስፋ ያረገው ክፉ ወጥመዱ ባዶ ውሎ ባዶ አደረ በአምላኬ እቅድ ተሰበረ ያሰበው አልተሳካም ያሰበው (፬x) ጳውሎስ ከባህር ላይ ከመርከብ አደጋ ወደዳሩ ደርሶ እንደተረጋጋ ብርድ ስለነበር እሳት እየሞቀ ድንገት ከእጁ ላይ በእባብ ተነደፈ ካሁን ካሁን አብጦ ይሞታል እያሉ እዛው ይቀበራል ብለው ሲወያዩ በእርጋታ መንፈስ እባቡን አራግፎ ጌታን አገልግሏል ከእፉኝት ተርፎ እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x) ለብዙ ለብዙ ዘመናት ጦር ከጁ ያልተለየው ወርውሮ ወርውሮ የማይስተው ሳኦል የተባለው ዳዊት ላይ ወርውሮ ለምንድነው የሳተው አዝኖለት አይደለም እግዚአብሔር ጋርዶት ነው ( 2x) እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection