አዝ፦ አርበኛ ነኝ (2x) የወንጌል አርበኛ ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (2x) አልፈራ አልደነግጥ ልቤም አይሸበር ጌታ ፍርሃቴን አድርጐታል ሰበር (አድርጐታል ሰበር) ጉልበታም መንፈሱ በእኔ ላይ ተለቋል ጠላቴ ይህን አይቶ ሁሌ ያንዣብባል ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል (ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል) እኔን ሊነካ ሲል እሳት ይቀድመዋል (2x) አዝ፦ አርበኛ ነኝ (2x) የወንጌል አርበኛ ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (2x) ቅጥሬ የእግዚአብሔር ጦር ደሞዜ በሰማይ ይሄ ስለሆነ ምንም ምንም አላይ (ምንም ምንም አላይ) በሃይል ተሞልቼ በብርቱ እዋጋለሁ ያዘዘኝን ጌታ ደስ ደስ ላሰኘው አዝ፦ አርበኛ ነኝ (2x) የወንጌል አርበኛ ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (2x) በጠቅላዩ ገዤ በኢየሱስ ታዝዤ ወደጠላት መንደር በመንፈስ ገስግሼ (በመንፈስ ገስግሼ) ጉድ ሳልሰራ አልመጣም በፍፁም በባዶ አየዋለሁ ጠላት በእሳት ቆስሎ ነዶ ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል (ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል) እኔን ሊነካ ሲል እሳት ይቀድመዋል (2x) ደግሞ ለጠላቴ እድል ፈንታ አልሰጥም ከደሊላ ጭን ላይ ተኝቼ አልገኝም (አልገኝም) የጌታዬ መንፈስ በእኔ ላይ ስላለ እንደወደደው ያድርገኝ እርሱ እንደፈለገ አዝ፦ አርበኛ ነኝ (2x) የወንጌል አርበኛ ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (2x)