አዝ፦ ለመዳን ቀንዴ ጌታዬ አምላኬ ያስነሳው ለእኔ ከአብ ጋር ያስተራረቀኝ ዘወትር ሚማልድልኝ ውዴ የመዳን ቀንዴ (4x) እነርሱ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዉ ካህናት የሆኑት ብዙዎች ናቸው እርሱ ግን ዘለዓለም ሚኖር ስለሆነ ዘወትር ይኖራል ለኤኔ እየማለደ አዝ፦ የመዳን ቀንዴ ጌታዬ አምላኬ ያስነሳው ለእኔ ከአብ ጋር ያስተራረቀኝ ዘወትር ሚማልድልኝ ውዴ የመዳን ቀንዴ (4x) በሚያገለግሉት በነቢያቱ አፍ የተነገረለት በዘመናት ምዕራፍ እንደተባለለት ድንገት ከተፍ አለ እግዚአብሔር ለአብራሃም በቃሉ እንደማለ ሊቀ-ካህን (4x) (አማላጄ) አማላጄ ለዘለዓለም ነው ወዳጄ (2x) የጥሉን ግድግዳ ላያዳግም አንዴ አፈራርሶ ጣለው ይህ የመዳን ቀንዴ ለእኔ ሆኖልኛል ታዳጊና ቤዛ በእውነት ኢየሱሴ ሃያል ነው ሲበዛ አዝ፦ የመዳን ቀንዴ ጌታዬ አምላኬ ያስነሳው ለእኔ ከአብ ጋር ያስተራረቀኝ ዘወትር ሚማልድልኝ ውዴ የመዳን ቀንዴ (4x) ይገርማል ሲነሳ ማንም አልጠበቀው ደም ግባት የሌለው ነበር የህማም ሰው ድንጌት ጥሶ ሄዶ እኔንም አስጣሰኝ ጠላትን ልመታው አሳልፎ ሰጠኝ ሊቀ-ካህን ሆኖልኛል ሊቀ-ካህን (2x) (አማላጄ) አማላጄ ለዘለዓለም ነው ወዳጄ (2x) ሊቀ-ካህን ሆኖልኛል ሊቀ-ካህን (2x) አማላጄ ለዘለዓለም ነው ወዳጄ (2x)