ማን ጠገበ (ዬ) ማን ረካ ቃላት ቢደረደር በዝማሬ ተርታ እኔ በበኩሌ አልረካሁም አንተን የሚገልጥ ቃል አላገኘሁም እንዲያውም ለክብርህ ባሉኝ ቃላቶቼ ላደናንቅህ እንጂ መቅደስህ ገብቼ (2x) እንካ ጌታ ጣፋጭ ምሥጋናዬን ስለአንተ ያለኝን ልግለጽ በዜማዬ (2x) ቃልህን ልከኸው በሕይወቴ ድንቅን ሰራ ከፊቴ ተነሳ የገዘፈው ያ ተራራ ታዲያ ለማመስገን ማን ከልክሎኝ ዝም እላለሁ ከልካይ የለብኝም ተፈትቼ አመልካለሁ (2x) ሌላ (4x) እንደአንተ ያለ የለም ሌላ (2x) የሚጤሰውን ጧፍ ሳታጠፋ ቅጥቅጡን ሸምበቆ ሳትሰብረው (2x) ድምጽን ሳታሰማ ትመጣለህ ፍጥረትን መገረም ትሞላለህ (2x) ልግባ ወደአንተ በአምልኮ በዐይኔ አሳይቶኛል ክንድህ ድንቅ ሰርቶ ተቀበለኝ ምሥጋናዬን ውዴ ለአንተ ያለኝን ይህን ስጦታዬን የአባቶች አምላክ ዘምርልሃለሁ አፌን ብቻ አይደለም ልቤን እሰጥሃለሁ (2x) የሚጤሰውን ጧፍ ሳታጠፋ ቅጥቅጡን ሸምበቆ ሳትሰብረው (2x) ድምጽን ሳታሰማ ትመጣለህ ፍጥረትን መገረም ትሞላለህ (2x) ማን ጠገበ (ዬ) ማን ረካ ቃላት ቢደረደር በዝማሬ ተርታ እኔ በበኩሌ አልረካሁም አንተን የሚገልጥ ቃል አላገኘሁም እንዲያውም ለክብርህ ባሉኝ ቃላቶቼ ላደናንቅህ እንጂ መቅደስህ ገብቼ (2x) ሌላ (4x) እንደአንተ ያለ የለም ሌላ (3x) ሌላ (2x) ሌላ (2x)