Song Lyrics

አልከሰርኩም

Endale Woldegiorgis
Yewengel Arbegna
አዝ፦ አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (2x) ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x) ማን ጠርቶ አፈረብህ አንገቱን ደፋብህ ቀና አልልም ብሎ ተሸማቀቀብህ እኔስ አላየሁም ከቶ አልሰማሁም ከፍ ከፍ አልኩ አንጂ አላሽቆለቆልኩም ሲወራ ሰምቼ ነበረ አሁን ግን ዓይኔ አይቷል ምሥጋናዬም ብሷል አዝ፦ አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (2x) ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x) እርሱማ ሞኝ ነው ጊዜውን ይፈጃል ኢየሱስ ኢየሱስ ሲል ዕድሜውን ይገፋል ቢሉኝ ከሰነፎች መንደር አንዳንዶቹ እንግዲህ ማዳኑን ያያል ዓይናቹህ በምድር መቶ እጥፍ በሰማይ የዘለዓለም ሕይወት አለኝ በኢየሱስ ቤት አዝ፦ አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (2x) ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x) ሞቅ ደመቅ ካሉ ከፈርዖን ቤት በንጉሠ ነገሥት ስልጣን ካለበት ጮማ ሲል ወይን ጠጅ ድሎት በሞላበት ብድራቱን ቆጥሮ ሙሴ አድርጓል ለቀቅ ለሁሉ እንደስራው ምትከፍል ነህና አምላኬ አረፈብህ ልቤ አዝ፦ አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (2x) ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x) እርሱማ ሞኝ ነው ጊዜውን ይፈጃል ኢየሱስ ኢየሱስ ሲል ዕድሜውን ይገፋል ቢሉኝ ከሰነፎች መንደር አንዳንዶቹ እንግዲህ ማዳኑን ያያል ዓይናቹህ በምድር መቶ እጥፍ በሰማይ የዘለዓለም ሕይወት አለኝ በኢየሱስ ቤት አዝ፦ አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (2x) ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x) ብሷል ምሥጋናዬ (3x) ብሷል ዝማሪዬ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection