ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ ልጁ አደረገኝ መንፈሱን ሰጥቶ ጌታ ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ አገልጋይ አደረገኝ በዘይት ቀብቶ ጌታ የቅባቱ ውፍረት ቀንበሬን ሰበረው (አሃሃ) የተጫነኝንም ሸክብ አወረደው (ኦሆሆ) እስራቴን ሁሉ የፈቱ እጆቹ የምለው የለኝም በእውነት ይባረኩ (2x) የጐልያድን ቁመት የልብሱን ክብደት (አሃሃ) አትኜ አይደለሁም የእርሱን የጦር ስልት (ኦሆሆ) ምንም አይደንቀኝም ጦሩና ጡሩሩ ወድቆ ይከሰከሳል በፊት በግንባሩ (2x) በእኔ ተማምኗል አስጥለዋለዉ ስሜንም አውቋል ጋርደዋለሁ አለና ጌታ በበቀል ወጥቶ ጠላቴን ጣለው እራሱን መቶ የረሳኸኝ መስሎት ጭፍራውን ሰብስቦ (አሃሃ) ውድቀቴን እንዲያዩ ወዳጆቹን ጠርቶ (ኦሆሆ) ጠአቱን ቀስሮ ጉድ እዩ ሲላቸው እኔን አአሰብክና ሃፍረት አለበስከው እህ (2x) ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ ልጁ አደረገኝ መንፈሱን ሰጥቶ ጌታ ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ አገልጋይ አደረገኝ በዘይት ቀብቶ ጌታ ፈርጠም ወፈር ያለ እልያብ እያለ (አሃሃ) በሰው የተናቀን ዳዊት ይቀብ ያለ (ኦሆሆ) መረሳቴን ሽሮ በኢየሱስ/በልጁ ያሰበኝ ምትክ የማይኖረው ለኔስ አምላክ አለኝ (2x) በእኔ ተማምኗል አስጥለዋለዉ ስሜንም አውቋል ጋርደዋለሁ አለና ጌታ በበቀል ወጥቶ ጠላቴን ጣለው እራሱን መቶ (2x)