Song Lyrics

አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ

በቀንና በሌሊት አንተን እፈልጋለሁ ልቤም አንተን አለ ደግሜ ደግሜ ኢየሱስ እልሃለሁ ልቤ አንተን አለ አዝ፦ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ እፎይ ምልብህ ውስጤ ያለውን ሁሉ ተንፍሼ በፊትህ ደስታ ሰላሜን ከልብስ ይልቅ ለብሼ ልቤ ከናፍቆት አንተን ከማለት አይቆጠብም ከአንተ ጋር መሆን ሚናፈቅ እንጂ አይጠገብም (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ ነህና ነህና የሕይወቴ ትርጉም ኢየሱስ ነህና ነህና የሕይወቴ ጣዕም ኢየሱስ (2x) ከገሃነም ጥርስ በአንተ መዳኔ በዝቶ ሳያንስ በተከበበም መሃል ከተማ ሰላም ስትሆን እረፍቴ እኮ ነህ ቅጥሬ እንዳይናድ በዓለም ሁካታ አብዝቼ እላለሁ አብረኸኝ ሆነህ ናፈቅከኝ ጌታ (2x) ነህና ነህና የሕይወቴ ትርጉም ኢየሱስ ነህና ነህና የሕይወቴ ጣዕም ኢየሱስ (2x) መሄድ መሄድ መሄድ ወዳንተ መገኛ ለነፍሴ ነውና ርሃቧ ቀና አልልም ሌሊት አልልም አብዝቼ እፈልግሃለሁ የሕይወቴ ትርጉም የመኖሬ አላማ አንተ ጋር ነው ያለው ኦ አንተን ጌታ እፈልግሃለሁ (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection