አንተን ሳስብ ጌታ አንተን ሳስብህ አንተን ሳስብ ገና አንተን ሳስብህ ወደ አምልኮ ባሕር ጠልቄ እሰጥማለሁ ወደ አንተ መገኛ አድራሻ እየገባሁ ስራዬ ስራዬ ማምለክ ነው በቅኔ አንተን መባረክ ነው ይሄው ጀመረኝ ለማመስገን በቅዱስ ስምህ በቋደሉ እንዲህ ይበሉ ከእኔ ጋራ አንተን ለማምለክ የወደዱ (2x) ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (4x) እንኳን እውነተኛ የሁሉም ባለቤት ሲከተል ልብ ያውቀው ሰው ያመልክ አይደል ወይ እስትንፋስ ከሌለው አምላክ አበጅቶ እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን ሚለው ቃል ከገባኝ ለክብርህ ልዘምር ከጣኦታት መንደር ክንድህ ስላወጣኝ አንተን ሳመልክህ ደስታ ቢያደርገኝ እንደሰከረ ይሄ ጥቂት ነው ከዚህ ይብሳል እየጨመረ ጌታ ሳመልክ ደስታ ቢያደርገኝ እንደሰከረ ይሄ ጥቂት ነው ከዚህ ይብሳል እየጨመረ ይሄው (4x) የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው ይሄው (4x) የአንተን አምልኮ ጌታ ኢሄው የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው የአንተን አምልኮ ጌታ ኢሄው የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው የአንተን ዝማሬ ጌታ ኢሄው አንተን ሳስብ ከጭንቀት ጐጆ ስር ወጥቼ በማመስገን ክንፍ እበራለሁ አንተን ሳስብ ከፍ ያለብኝን በሙሉ ወደታች ማየት እጀምራለሁ አንተን ሳስብ ማጉረምረም ግቢ እኮ አይደለም ውሎ ማደሪያ ሰፈሬ አንተን ሳስብ ጌጠኛ ልብሴን ለብሼ ቅዱስ ነው ሚልህ መዝሙሬ ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (4x) ነፍሥም አይቀርልኝ የአንተን ማንነት ክብርህን አስቤ ቅዱስ ሊል ይፈጥናል ታላቅነትህን ሊያመሰግን ልቤ የምሥጋና ሽቶ ሳልቆጥብ ሳልሰስት ለክብርህ ላፍሰው እንኳን ለደቂቃው ሰዓቱን ባመልክህ ሲያንስህ ነው የሰራኸኝ የፈጠርከኝ ለዚህ ነውና ፈጽሞ አልጠግብም ዘምሬ አውርቼ የአንተን ምሥጋና (2x) አንተን ሳስብ ከጭንቀት ጐጆ ስር ወጥቼ በማመስገን ክንፍ እበራለሁ አንተን ሳስብ ከፍ ያለብኝን በሙሉ ወደታች ማየት እጀምራለሁ አንተን ሳስብ ማጉረምረም ግቢ እኮ አይደለም ውሎ ማደሪያ ሰፈሬ አንተን ሳስብ ጌጠኛ ልብሴን ለብሼ ቅዱስ ነው ሚልህ መዝሙሬ ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (4x)