አመልክሃለሁ (4x) ትምክቴ ነህ የኩራቴ ጥግ ትምክቴ ነህ ያለኸኝ ማዕረግ (2x) አሁንም ላምልክህ ላምልክህ (4x) የጨዋታዬ መነሻ ርሶ ጌታዬ አንተ ነህ አልፎም ንኡሱ የዕድሜ ልኬ ስብከት ትምህርት ኩራቴ አንተ ነህ የማልታክትህ ስነሳም በአንተ ስቀመጥ በአንተ ስጀምር በአንተ ስጨርስ በአንተ ኢየሱስ የእኔ ስብከት ኢየሱስ የእኔ ትምህርት (2x) አንተን አደብዝዞ አዜብ የሚሆንብኝ የፍርህን ምስል የሚያጨልምብኝ ይውጣ ከጓዳዬ በእሳት መጥረጊያ አልፎ አይውጠኝም የሥምህን መዝጊያ ኢየሱስ የሚለውን እርስ አልቀይርም በሚጠፋው ዓለም ጌጤን አልሸፍንም ልቤ አይሸፍትም ፍቅርህ ላይ ዘምኖ ይህ ልብ ብሶበታል መሮጥ አንተን ብሎ ስነሳም በአንተ ስቀመጥ በአንተ ስጀምር በአንተ ስጨርስ በአንተ ኢየሱስ የእኔ ስብከት ኢየሱስ የእኔ ትምህርት (2x)