ተመስገን የልቤ ፈውስ የልቤ ጠጋኝ (4x) ክብር ይሁን የማጽናናትህ ደመና ክብር ይሁን ዙራዬን ከቦታልና ክብር ይሁን ሚያቋርጥ አይደል ደስታዬ ክብር ይሁን ምንጩ አንተ ነህ ጌታዬ የልቤ ጉልበት ይንበረከካል ገብተህ ላከምከው ክብር ይሰጣል ክብር ይሁንልህ (2x) ክብር ይሁንልህ (4x) እሩቅ ነው መንገዱ ይለቤ አድራሻ ሰው አይደርስበትም ይቆማል ውጪው ጋር (2x) ልቤ ቢቆስልብኝ አካሚው አንተ ነህ ከደጅ የማትቆም የምትገባ ዘልቀህ ከደጅ የማትቆም የምትገባ ዘልቀህ ክብር ይሁንልህ (4x) ማን አለኝ (2x) ከፊቴ እያለፈ የልቤን የሚረዳ ዘልቆስ የሚጐበኝ የመንፈሴን ጓዳ አንተ ብቻ ነህ ለልቤ መክፈቻ ያለህ አንተ ብቻ ነህ ለውስጤ መክፈቻ ያለህ ክብር ይሁን የማጽናናትህ ደመና ክብር ይሁን ዙራዬን ከቦታልና ክብር ይሁን ሚያቋርጥ አይደል ደስታዬ ክብር ይሁን ምንጩ አንተ ነህ ጌታዬ የልቤ ጉልበት ይንበረከካል ገብተህ ላከምከው ክብር ይሰጣል ክብር ይሁንልህ (2x) ክብር ይሁንልህ (4x)