Song Lyrics

ሕያው ምንጭ

ሸቶናል የአንተ መገኘት ሸቶኛል ሸቶኛል የአንተ ህልውና ሸቶኛል እለመልማለሁ ብዙ አፈራለሁ እለመልማለሁ ብዙ አፈራለሁ አዝ፦ አልደርቅም አልደርቅም ሕያው ምንጭ አንተ አለኸኝ ኢየሱስ (2x) ዛፍ እንኳ ቢቆረጥ ደግሞ ሊያቆጠቁጥ አዲስን ቅርንጫፍ ሊያበቅል ተስፋ አለው ለፍጥረት የመታደስን ይህ እንደገና ተስፋን ሰጠኸው ለእኔማ አንተ ነህ ለእኔ የነፍሴ ተስፋ የምትበልጥ ለማቆጥቆጤ ከውኃ ሸታ የክፉ ሳር ቆርጦ ቢጥለኝ እስከወዲያኛው ከአንተ ሊለየኝ ስመታ ተንገዳግጄ ስደርስ ወደታች ስቧጥጥ ሲብስ ማቃሰት ሆኖብኝ አንዳች ሲሸተኝ የመገኘትህ የአንተ መዓዛ ቆማለሁ ዳግም በጽኑ ምህረት ሲበዛ (2x) አዝ፦ አልደርቅም አልደርቅም ሕያው ምንጭ አንተ አለኸኝ ኢየሱስ (2x) በድርቅ ዘመን ከቶ እንዳልሰጋ ፍሬ ማፍራቴን ላይቆም አንዱ ጋር እምነቴ አንተ ነህ መታመኛዬ ሙቀት ሲመጣ ላይፈራው ልቤ ከአንተ አጠገብ ተተክያለሁ ስለዚህ ሕይወቴ ሁሌ ለምለም ነው (2x) ሁሌ ለምለም ነው ለመልማለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection