አዝ፦ እኔማ እንዴት ላውራው እንዴት ልተርከው ኦሆ (2x) የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው ከእርሱ ጋር ስንጓዝ ባሳለፍኳቸው ዓመታት ተለይቶኝ አያውቅም ለሰከንድ እንኳን ለሰዓት ከእስትንፋሴ ይልቅ አምላኬ ለእኔ ቅርቤ ነው ኢየሱሴ ለእኔ ሁልጊዜ ለእኔ ታማኝ ነው አዝ፦ እኔማ እንዴት ላውራው እንዴት ልተርከው ኦሆ (2x) የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው ሺህ ቃላቶች አይገልፁትም የጌታዬን ቸርነት ምህረቱ እጅግ ብዙ ልክ የለው ታማኝነቱ ጥቂት አልቆጥብም ባለኝ ኃይሌ እዘምራለሁ ክብር የኢየሱስ ነው ክብርን እሰጠዋለሁ አዝ፦ እኔማ እንዴት ላውራው እንዴት ልተርከው ኦሆ (2x) የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው ጌታ አምላኬ ይሄ ነው መኩራሪያ የምታመንበት ኢየሱስ ብዬ ጠርቼው ምንጊዜም የማላፍርበት ምህረቱን ልዘምር ፍቅሩን ደግሞ ተዓምራቱን ሞገሱን በላዬ አፍሶታል በረከቱን አዝ፦ እኔማ እንዴት ላውራው እንዴት ልተርከው ኦሆ (2x) የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው