Song Lyrics

የፍቅር መዓዛ

YEFIKER MEAZA

ኢየሱስ ልዩ ነው ልዩ ነው ሚመስለው የሌለ በሰማይ በምድር ግርማው የደመቀ ላውራ ልናገር ምህርቱን ፍቅር እንደሆነ የአለሙ ቤዛ ስሙ የገነነ አልሻም ሌላውን የዚህን አለም ክብር ለነፍስ ጉድለት እንጂ ጥቅም የሌለውን የዘላለም ህይወት የዘላለም ደስታ የእግዚአብሔር ልጅ የእኔ እርካታ 1.የፍቅር መዓዛ የምህረት ሽታ የነፍስ ልምላሜ የመንፈስ እርካታ ኢየሱስ የሚባል ወዳጅ አለኝ እኔ የዚህ አለም ግብዣ ለምኔ ለምኔ 2.ጉም አይዘገንም ባዶ ከንቱ ተስፋ ምኞቱ ወጥመዱ ፅንሱ ለሃጢያት በሽታ መርዙ አደገኛ ነው ሳይገድል መች ይለቃል ኢየሱስን ያገኘ ማርከሻውን አውቋል 3.የደመቀ ብርሃን ሰላም የሞላበት የጣፈጠ ህይወት ኢየሱስ ያለበት እግዚአብሔር የያዘው የተደላደለ ይሄ ነው ይሄ ነው እጅግ የታደለ 4.ምን ቢበዛ ንዋይ አይተኛም ልብ አርፎ የእፎይታ ርቀቱን እያቀረበው ስቦ የዘላለም ክብር ደስታ የሞላበት ኢየሱስ ኢየሱስ የህይወት መሰረት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection