እረፍት ያለበት ሰላም የሞላበት እግዚአብሔር በልጁ እኔን የጠራበት ልቤን ሰጥቼ እንዳገለግለው ከጨለማ አለም ጌታ ነጥቆ አወጣኝ አንዴ ወዶኛል አንድ ልጁን ሰጥቶ የጨለመውን ልቤን አብርቶ ጌታ ይዞኛል ከአምላኬ እጅ ነጥቆ ማን ያወጣኛል ጊዜ የማይሽረው ዘመን ማይለውጠው ባፈሰሰው መንፈስ ልቤን የሚያሞቀው የሚያዘምረኝ በቀንም በማታ የኢየሱስ ፍቅር ይዞኝ ነክቶኝ ነው ጌታ አንዴ ወዶኛል አንድ ልጁን ሰጥቶ የጨለመውን ልቤን አብርቶ ጌታ ይዞኛል ከአምላኬ እጅ ነጥቆ ማን ያወጣኛል