ሀጥያቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ አምላኬ ደግ ነህና ምህረት እሻለሁ ኦሆሆ ቀድሰኝ እቀድሳለሁ ትህትናን ከጌታ ተምሬ ነበረ ወዶ ዝቅ ማለት እሱን ካከበረ አንደኛ ካላሉኝ አሁን ይከፋኛል እባክህ አምላኬ ሆይ ምህረትህ ያሻኛል እባክህ የኔ ጌታ ትህትናህ ያሻኛል ዝቅ ዝቅ ያለው ከሰማያቱ በክብር ሳለ በአምላክነቱ ይህን ምሳሌውን ከሱ ተምሬ የጌታን መንገድ ልኑረው ዛሬ ልኑረው ዛሬ ልኑረው ዛሬ ሀጥያቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ አምላኬ ደግ ነህና ምህረት እሻለሁ ኦሆሆ ቀድሰኝ እቀድሳለሁ ለእርቅ አሻፈረኝ እምቢ ያለው ልቤ ከየት ተምሮት ነው የገዛው ሀሳቤን ከየት ሾልኮ ገባ ጥላቻ ከውስጤ ይቅርብኝ ትቻለሁ ይበልጣል ወንድሜ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የቃሉ መንገድ ይቅር እንዳለኝ ይቅር የምልበት እንደ መሃሪው እንደ አለኝታዬ ልቤ ይሁንልኝ እንደ ጌታዬ እንደ ጌታዬ እንደ ጌታዬ ሀጥያቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ አምላኬ ደግ ነህና ምህረት እሻለሁ ኦሆሆ ቀድሰኝ እቀድሳለሁ የክፋት መሠረት አፍቅሮተ ነዋይ አይኔን አይጋርድብኝ ጌታዬን እንዳላይ በምላሴ ጡንቻ ይቅር መታመኔ መመካት በእግዚአብሔር ይሁንልኝ ለኔ መመካት በእግዚአብሔር ይሁንልኝ ለኔ በሃብቱ ብዛት ላይሆን ሕይወቱ ለዚህ አለም ረብ ሰው መጎምጀቱ ጥቂቱን ነገር የምትባርከው ባንተ ላይ ይሁን ልቤ ማረፊያው ልቤ ማረፊያው ልቤ ማረፊያው ሀጥያቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ አምላኬ ደግ ነህና ምህረት እሻለሁ ኦሆሆ ቀድሰኝ እቀድሳለሁ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝና እንደ ርህራሄህ ብዛት አንጻኝና ክቡር በሆነው ደም እጠበኝ ልቀደስ ይዳሰኝ መንፈስህ ይንካኝ ውስጤን ያድስ /2/ ልቤ ተሞልቶ በድነት ደስታ ልዘምርልህ ለስምህ ጌታ የመገኘትህ ክብር ይውረሰኝ በቀን በማታ ሳመልክህ ልገኝ ሳመልክህ ልገኝ ሳመልክህ ልገኝ ሀጥያቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ አምላኬ ደግ ነህና ምህረት እሻለሁ ኦሆሆ ቀድሰኝ እቀድሳለሁ