Song Lyrics

ለእኔ ክብሬ

Daniel Amdemichael
Yesew Iji Yelelebet
አዝ፦ እግዚአብሔር ነው ለእኔ ክብሬ ውበት ሞገስ ዘውድ አክሊሌ (2x) ከቶ የማይርቅ በፍፁም ከአጠገቤ ሚራራልኝ ክብሬ ነው ጥጋቤ አይጓደል በፍፁም ምሥጋናዉ ሥሙ ይክበር ይድነቅ እልልታው በቅዱሳን ጉባኤ ህብረት መሆን ሊመሰገን ሊከብር ይገባዋል መልካም መዓዛ ሆኖ ያርግ መሥዋዕቴ ለወደደኝ አፍቃሪ መድሃኒቴ ይድመቅ ጭብጨባው ይድመቅ ዕልልታውም ይሰማ ምሥጋና በአሪያም ክብር ለእርሱ ነውና (2x) የአገኘሁት ደህንነት ለመንፈሴ ዳግም ልደት በደሙ መቀደሴ የአምላክ መንግሥት ወራሽ አድርጐኛል ባመሰግን ብዘምር ያንስብናል ኦ ትበል ዛሬ ነፍሴ ታምጣ ለእርሱ ምሥጋና ውዳሴ ለንጉሡ ጌታ ድንቅ ነውና (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ነው ለእኔ ክብሬ ውበት ሞገስ ዘውድ አክሊሌ (2x) ከቶ የማይርቅ በፍፁም ከአጠገቤ ሚራራልኝ ክብሬ ነው ጥጋቤ አይጓደል በፍፁም ምሥጋናዉ ሥሙ ይክበር ይድነቅ . (1) . ይዘምራል ጌታ ነው ክብሬ እያለ በአምላኩ ሰው መሆኑን ያስተዋለ ሕይወት የለውም ከጌታ ኢየሱስ ሌላ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የእርሱ ተድላ ይድመቅ ጭብጨባው ይድመቅ ዕልልታውም ይሰማ ምሥጋና በአሪያም ክብር ለእርሱ ነውና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection