Song Lyrics

አላማርረውም

አዝ፦ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (2x) አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል አዝ፦ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (2x) ሁልጊዜ መንገዱ በፊቴ አጸናለሁ እግሬን በቤቱ ለእኔስ ፍቅሩ ይበቃኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል እርሱ ነው የእኔ እድል ፈንታ እርስቴ የሕይወቴ መከታ ሁልጊዜ በእርሱ ደስ ይለኛል ከሁሉ ፍቅሩ በልጦብኛል አዝ፦ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (2x) አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል የሰው ፍላጐቱ ብዙ ነው የእግዚአብሔርን ፍቃድ እስኪለየው በልቤ ብዙ ሃሳብ ይኖራል የእግዚአብሔር የሆነው ይፀናል ይፀናልኝ ለእኔስ የእርሱ ሃሳብ ፈቃድን ለመጣስ አልሻም ሃሳቤን የእርሱ ሃሳብ ይወረሰው ሲገለጥ ሁሉም ለበጐ ነው ተግቶ ለጠበቀው ጌታ ሲሰጥ ምላሽን ለምን ተስፋ ልቁረጥ ሳልበልጠው በትንሽ መታገስ ጥሩ ነው ብዙ ድንቅን ያሳያል ፀንቶ የጠበቀ መልካም ፍሬ ይበላል ከሁሉ የበለጠ ክብሩን አይቻለሁ ወደር የለሽ ፍቅሩን ምሕረት አግኝቻለሁ በትልቅ ትንሽ እንዴት አማርራለሁ የተደረገልኝ እጅግ እጅግ ብዙ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection