Song Lyrics

እጅግ ያኮራኛል

አዝ፦ እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው ክብርህን ላውራው ልናገረው በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኸው ነው ፍቅርህ ከሁሉም በላይ በልጦብኛል እንዳመልክህ ሁል ጊዜ ግድ ይለኛል እንዴት ብዬ የሆዴን ልናገረው ተመስገን ከማለት ሌላ ቃላት አጣሁ እንዴት ብዬ የሆዴን ልናገረው ምሥጋናዬ ምሥጋና ማደሪያህን ይሙላው እንዴት ብዬ የሆዴን ልናገረው ምሥጋናዬ ምሥጋና ማደሪያህን ይሙላው አዝ፦ እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው ክብርህን ላውራው ልናገረው በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኸው ነው ዛሬማ ሰው አድርጐኛል ድንቅ ፍቅርህ ሞገስ ሆኖኛል ጌታ ክቡር ሥምህ በውዳሴ የተሞላ በምሥጋና መዝሙር ይዘመርልህ የአንተ ነውና በፈቃዴ ውዳሴን እጨምራለሁ መድሃኒቴ ጌታዬ ነህ አነግስሃለሁ (2x) አዝ፦ እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው ክብርህን ላውራው ልናገረው በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝንላሰማ ምሥጋና ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኸው ነው ሁሉ በአንተ የሆነ ያማረለት ከአምላኩ ጋር መንገዱ የቀናለት ኧረ እንደ እኔ ማን አለ ቸር ጌታዬ ክቡርሥምህን ልባርከው በዜማዬ ክቡር ሥምህን እምላኬ ዛሬም ልባርከው መድሃኒቴ እና ጌታዬ ነህ አነግስሃለሁ አዝ፦ እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው ክብርህን ላውራው ልናገረው በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኸው ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection