Song Lyrics

ካረካህ

ምነው ከዚህ በላይ አሃሃ ልቤ ቢሆንልኝ ኦሆሆ በቅኔ ተሞልቶ አሃሃ ፊትህ ቢፈስልኝ ኦሆሆ አንተ ካደረግኸኝ አሃሃ የአንተ የክብር እቃ አሃሃ ኢየሱሴ ተመስገን ኦሆሆ ምሥጋናዬን እንካ አሃሃ አዝ፦ ካረካህ ከወደድከው ምሥጋናዬ ካስደሰተህ አምላኬ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ ወዳጄ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ ምህረትና ፀጋ አሃሃ ፍቅር የበዛለት ኦሆሆ ኧረ እንደ እኔ ማነው አሃሃ መልካም ያደረግህለት ኦሆሆ አንተ ደስ ካለህ አሃሃ ካረካህ ምሥጋናዬ ኤሄሄ እገዛልሃለሁ የእኔ ጌታዬ በሁለንተናዬ ኤሄሄ አዝ፦ ካረካህ ከወደድከው ምሥጋናዬ ካስደሰተህ አምላኬ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ ወዳጄ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ መቅደስህ ባለበት አሃሃ ክብርህ በሞላበት ኦሆሆ እንዴት ደስ ያሰኛል የእኔ ጌታ ለሥምህ መቀኘት ኦሆሆ ስምህ ሞገሴ ነው አሃሃ መገኘትህ ፈውሴ ኤሄሄ አክብሮትን ታብዛ አሃሃ ታመስግንህ ነብሴ ኤሄሄ አዝ፦ ካረካህ ከወደድከው ምሥጋናዬ ካስደሰተህ አምላኬ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ ወዳጄ ሆይ በየዕለቱ ለሥምህ ክብር ይሁንልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection