Song Lyrics

ይገርማል

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ የሁሉ መድሃኒት በቸርነት እየደገፍክ ታኖረኛለህ በሕይወት ምስክር ነኝ ለሰራኸው ብዙ ተዓምር አይቼአለሁ አምላኬ ሆይ ስለ ፍቅርህ በየዕእለቱ እደነቃለሁ አዝ፦ ይገርማል የአንተ ምህረት ይገርማል የአንተ ፍቅር ይገርማል የአንተ ሥራ ያኖረኛል ከአንተ ጋራ ያኖረኛል ከአንተ ጋራ አቁሞኛል ከአንተ ጋራ አቁሞኛል ከአንተ ጋራ (2x) ቀኑን ስትጠብቀኝ ውለህ ጌታ ሌሊቱን አትተኛ በመውጣቴ በመግባቴ ሆነኸኛል ቸር እረኛ መች ያልቅና የአንተ ሥራ በየዓይነቱ ብዘረዝር ቃል አጣሁ እጄን በአፌ ጭኜ ከመደነቅ በቀር አዝ፦ ይገርማል የአንተ ምህረት ይገርማል የአንተ ፍቅር ይገርማል የአንተ ሥራ ያኖረኛል ከአንተ ጋራ ያኖረኛል ከአንተ ጋራ አቁሞኛል ከአንተ ጋራ አቁሞኛል ከአንተ ጋራ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection