አዝ፦ ሲነጋም ሲመሽም ሁልጊዜ የማስታውሰው ከልቤ የማይጠፋው ዘለዓለማዊውፍቅርህ ነው (2x) እንዴት ይረሳል ያደረግህልኝ? በቀራንዮ የከፈልክልኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዛሬም ትኩስ ነው ግን ቃል አጠረኝ እንዳልተርከው (ብዘምር ቃላቶች ያጥሩኛል ብናገር ቃላቶች ያጥሩኛል ለፍቅርህ ምን ምላሽ ይገኛል ኦሆሆ) 2x አዝ፦ ሲነጋም ሲመሽም ሁልጊዜ የማስታውሰው ከልቤ የማይጠፋው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ነው (2x) አይታክተኝም ለሃገር ባወራ ስለ አንተ ክብር ስለ አንተ ዝና ምነው በሆነ ልቤ እንደ ጅረት እንደ ውኃ ፈሳሽ እንደ ገነት ምንጭ (አምልኮ ማደሪያህን ይሙላው ዝማሬ ማደሪያህን ይሙላው ዕልልታ ማደሪያህን ይሙላው ኦሆሆ) 2x አዝ፦ ሲነጋም ሲመሽም ሁልጊዜ የማስታውሰው ከልቤ የማይጠፋው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ነው (2x)