Song Lyrics

ይሆናል

አዝ፦ አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (2x) የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ ዛሬስ አስደነቀኝ (2x) ይገርማል ይደንቀኛል የእርሱ ሥራ የትኛው የቱን ትቼ የቱን ላውራ (2x) በቀንም በምሽትም በሌሊቱ ምሥጋና ይድረሰው በየዕለቱ (2x) አዝ፦ አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (2x) የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ ዛሬስ አስደነቀኝ (2x) ያለውን የሚፈፅም የማይረሳ በቃሉ ታማኝ ነው የእኔ ጌታ (2x) በጊዜው ከተፍ የሚል የሚደርስ እኔም ዛሬ ቆሜ ሥሙን ልወድስ (2x) ይሆናል እርሱ/ጌታ ያለው ይሆናል ሰው በከንቱ ኧረ ለምን ይጨነቃል እግዚአብሔር ያለው ይሆናል (2x) አዝ፦ አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (2x) የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ ዛሬስ አስደነቀኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection