Song Lyrics

በአምላኬ

Daniel Amdemichael
Yesew Iji Yelelebet
አዝ፦ በአምላኬ በስራው ከምደነቅ በቀር በቂ ቃላት የለኝም ዘርዝሬ እንዳልናገር (2x) ሺ ቃላት ደርድሬ በሺ ቃላት ባወራው የአምላኬ ቸርነት ከዚያም በላይ በላይ ነው ዝም ብዬ ሁሌ አመሰግናለሁ እርሱ በሰጠኝ ፀጋ መልሼ አከብረዋለሁ ለአምላኬ ምሥጋናው ብዙ ነው በደስታ ቆሜ ላመስግነው የዕልልታው ድምጽ በቤቱ ይሰማ ውዳሴ ለሆነው ገናና ክብርም ለእርሱ ነውና ይደርደር በገናው ይድመቅ ዕልልታው ይሰማ የጌታን ክብር ላወራ ቆሜያለሁ እኔማ በጐነቱን እንድናገር አምላኬ መርጦኛል ለእርሱ መለየቴን ሳስብ ምሥጋና ሞልቶኛል ምህረቱ ከአእምሮ በላይ ነው ይቅርታው . (1) . የሌለው ያመልካል ብዙ የተተወለት ይወዳል ምህረት የበዛለት አምላክ ድንቅ ያደረገለት ይሰበር ሽቶ ብልቃጡ መዓዛው ያወደው ከእግሮቹ ስር ዝቅ ብዬ ጌታዬን ላምልከው ግድ የለም ዙሪያ . (2) . በእኔ ግር ቢለው ምን ያህል እንደወደደኝ እኔ ነኝ የማውቀው አዝ፦ በአምላኬ/በጌታዬ በስራው ከምደነቅ በቀር በቂ ቃላት የለኝም ዘርዝሬ እንዳልናገር (2x) ሺህ ቃላት ደርድሬ በሺ ቃላት ባወራው የአምላኬ ቸርነት ከዚያም በላይ በላይ ነው ዝም ብዬ ሁሌ አመሰግናለሁ እርሱ በሰጠኝ ፀጋ መልሼ አከብረዋለሁ በፍቅሩ እጆቼን ይዞኛል አይደክምም ሁሌ ይታገሰኛል ኢየሱስ ኢየሱስ ልበለው መድሃኒት ለነፍሴ ፈውስ ነው ክብር ታማኝ ለሆነው ይክበር የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ ውዳሴ በሠማይ በምድር በታላቅ ዕልልታ እስትንፋስ ያለው ይዘምር ይውጣ ምሥጋናዉ በአባቱ ቀኝ በላይ ከብሮ ጌታ ለሆነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection