ጌታ በሕይወቴ ውዱ ያደረገውን መቼም አልረሳውም እርሱ በሕይወቴ ፈቅዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም አልረሳውም ያደረገልኝን አልረሳውም ለእኔ የሆነልኝን አልረሳውም የአምላኬን ውለታ ዘወትር ልቀኝ ለሚያኖረኝ በደስታ ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው ያኔ በመከራ የደገፈኝ ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው (2x) ይሁን ያለው ሁሉ ይሆናል ሃሳቡን ማን ይከለክላል እንዴት ልርሳ መልካምነቱን ልዘምር እንጂ ምህረቱን ተስፋ ላጣ ተስፋ ነው ለምስኪኑ ወዳጅ ላጣ ብቸኛ ነው ወገኑ ላመስግነው እንጂ እኔ ልወድሰው ኃይሌ ክብሬ ታሪኬም ኢየሱስ ነው ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው ያኔ በመከራ የደገፈኝ ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው ዮሴፍን ከእስር ቤት ያወጣ ለሹመት ሽልማት ያበቃ የዳንኤል አምላክ ተዐምረኛ ከአንበሶኝ የሚያድን ከበላተኛ አይገርምም ወይ ይሞታል የተባለው ሕይወት ዘርቶ በግሩ ቆሞ አየነው የቀመሰ ያውቀዋል የእርሱን ማዳን የተነካ በእግዚአብሔር ብርሃን ጌታ በሕይወቴ ወዶ ያደረገውን መጄም አልረሳውም