የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ የይሁድ አንበሳ የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምባ ላይ ፈረስ የምትቀመጠው በክብር በግርማም የምትመለሰው የዘለዓለም ተስፋችን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የደህንነታችን ራስ(1) . አዝ፦ ይገባሃልና (3x) ኦሆ ይገባሃልና (3x) ኦሆ ፊትህ እንደፀሐይ በሃይል ያበራል ፍቅርህ ከዕንቁ ይልቅ ልብን ይማርካል ውበትህ ያማረ ክብርህን ተላብሰሃል ተመስገን ጌታችን ተባረክ ብለናል በምድር ክበር በሠማይ ይገባሃልና ንገሥ ከሁሉም በላይ አዝ፦ ይገባሃልና (3x) ኦሆ ይገባሃልና (3x) ኦሆ ብዙዎች ተገዙ ፍቅርህን ተረድተው እንደ እግዚአብሔር ያላ ማንም የለም ብለው ድምጻቸው ተሰማ ከየማዕዘኑ ቅኔን ተቀኙልህ በስምህ የዳኑ ተመስገን ተባረክ ብለው ዘምረው አይጠግቡም ደስታህ መብላቸው ነው አዝ፦ ይገባሃልና (3x) ኦሆ ይገባሃልና (3x) ኦሆ