Song Lyrics

ዓለም አታላይ

Daniel Amdemichael
Yesew Iji Yelelebet
ዓለሙም ምኞቱም አንድ ላይ ጠፊ ነው (2x) ዘለዓለም የሚያኖር የጌታን ፍቃዱን ማድረግ ነው (2x) አትታለል ልቤ በሚያብለጨልጨው ከክፋቱ/ከአመጹ ጋራ ይህ ዓለም ጠፊ ነው (2x) አዝ፦ ዓለም ዓለም አታልይ ናት (2x) እውነት ሕይወትና መንገድ ጌታ ኦ ለታመኑበት (2x) ከእሳት ተጠብቆ ለሚቆየው ዓለም (2x) ነፍሴ አትጓጊለት በፍፁም ይቅርብሽ ግድየለም (2x) ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እርሱ ብቻ ከእሳት ከጨለማው በእምነት ማምለጫ (2x) አዝ፦ ዓለም ዓለም አታልይ ናት (2x) እውነት ሕይወትና መንገድ ጌታ ኦ ለታመኑበት (2x) ሕይወትና ተስፋ የዘለዓለም ደስታ (2x) በእውነት ለታመኑበት የሚሰጥ ከጌታ (2x) ይህን ያስተዋለ ጌታን ሙጥኝ ይላል ከዚህ ዓለም እድፈት እራሱን ያነጿል (2x) ዓለምን አትርፎ ሰው ነፍሱን ቢያጐድላት ከቶ ምን ሊጠቅመው ሁሌ ላይኖርባት ብልጭልጯን ንቆ እንደ ቃሉ የኖረ እርሱ ነው ጠቢብ ሰው ያ ነው የተማረ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection