ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ኦሆ ጽኑ መሰረቴ የነፍሴ መከታ የራራልኝ ቀድሞ በፍቅሩ የሳበኝ ጨለማዬን ገፎጭ በብርሃን ያኖረኝ ቅኔን ጨመረልኝ በአፌ ለክብሩ እንድዘምር ከልቤ ምሥጋናውን ደግሞ እንዳወራ አብሬ እንዳመልከው ከቅዱሳን ጋራ ከአሪያም ወረደ መንፈሱ ልቤን አደረገው መቅደሱ አቤት የአምላክ ፍቅር ምህረቱ ኢኸው ልጅ አደረገኝ እንድኖር በቤቱ ከቁጥር ያለፈ ቸርነት ሠማያዊ ፀጋን አሄ አምላኬ ሰጥቶኛል የዘለዓለም ሕይወት ማዳኑን በእኔ ላይ ገለጠ በደሙ ቀደሰኝ አሄ ኢየሱስ ሕይወቴን መልካም አደረገ ምድር እልል ትበል ለንጉሡ ሠማይም ያጨብጭብ ለቅዱሱ ሁሉንም በኃይሉ የፈጠረው የዘለዓለም ዓለም መንግሥት የእግዚአብሔር ነው ማዳኑን ልዘምር ከፍ ላድርገው ከምርጦቹ ጋራ ላመስግነው የጠለቀ ፍቅሩንም ልናገር ከሠማይ በምድር ታላቅ ስሙ ይክበር ፍቅሩን አፈሰሰ ማዳኑን ገለጠ እህ በመስቀል ላይ ሞቶ ምህረቱን አወጀ እርሱን ያመነች ነፍ በሕይወት ትኖር ዘንድ ቤዛ ለዓለሙ ሆነ የኀጢአት መሥዋዕት ሞትን ያሸነፈ ግድለኛ ማኅተሙን የፈታ ኃይለኛ የነገሥታት ንጉሥ አንበሳ ምሥጋና የሚገባው ክብርና ሙገሳ የጌቶቹ ጌታ ግርማዊ መንግሥት ከላይ ነው ሠማያዊ ፍጥረት በመገዛት የሚያከብረው የዓለም መድሃኒት ኢየሱስ ጌታ ነው አቻ ይገኝለት መውደዱ አቤት የአምላክ ፍቅር አሄ ከአእምሮ በላይ ነው ምህረት ተገዝቶ አሄ ምክሩ ከሰው ጥበብ የላቀ ማስተዋሉ ረቂቅ አሄ ይሄ ነው ጌታችን በክብር የደመቀ ሃሌሉያ ልበል ላመስግነው ኃይልና ጥበብም የእግዚአብሔር ነው ሃሴት ታደርጋለች ዘወትር ነፍሴ ሁሌ እያቀረበች ክብርና ውዳሴ ክብር ለሚገባው ክብር ይሁን በዙፋኑ ላለው ኦ ልዘምር ለአማልክት አምላክ ይሁን ስግደት በሠማይ በምድር ኃይልና በረከት ሃሌሉያ ልበል ላመስግነው ኃይልና ጥበብም የእግዚአብሔር ነው ሃሴት ታደርጋለች ዘወትር ነፍሴ ሁሌ እያቀረበች ክብርና ውዳሴ ክብር ለሚገባው ክብር ይሁን በዙፋኑ ላለው ኦ ልዘምር ለአማልክት አምላክ ይሁን ስግደት በሠማይ በምድር ኃይልና በረከት አምልኮና ስግደት ይሁንለት አምልኮ ስግደት ይሁንለት ለንጉሡ ለንጉሡ