አዝ፦ ይገርመኛል የአምላኬ ፍቅር ቸርነቱን አልታክትም ሁሌ ባወራው ምህረቱን እርሱ በሰራው ጸድቅ እኔን ያኖረኛል ስለመዳኔ ላከብረው ይገባኛል ኦሆ ላመስግነው ከፍ ላድርገው ክብርን ልስጠው ኦሆ በሠማዩ መዝገብ ስሜን ስለጻፈው ደስ ይለኛል ጸድቄአለሁኝ በእርሱ ስራ ኦሆ እኖራለሁ ድንቁን ታሪኩን ሳወራ ኢየሱስ መድህኒ እማረፊያ ሆኖናል ከሞት ከጨለማ መንጥቆ አውጥቶኛል የከበረ ስሙን ዘወትር እየጠራሁ ቅኔን እቀኛልሁ በታላቅ ጉባኤ በልጆቹ መሃል አመሰግናለሁ በልጆቹ መሃል አመሰግናለሁ (3x) አመሰግናለሁ ተመስገን ትላለች እርሱ ያዳናት ነፍሴ ሳመልከው ደስ አለኝ በእውነት በመንፈሴ አድናቆቴም ይኸው አክብሮቴም ይኸው ፊቱ ልስገድለት ለጌቶቹ ጌታ ለነገሥታት ንጉሥ ሞገስ ይሁንለት ለጌቶቹ ጌት አሞገስ ይሁንለት ሞግስ ይሁንለት ለነገሥታት ንጉሥ ለጌትቹ ጌታ ሞገስ ይሁንለት አዝ፦ ይገርመኛል የአምላኬ ፍቅር ቸርነቱን አልታክትም ሁሌ ባወራው ምህረቱን እርሱ በሰራው ጸድቅ እኔን ያኖረኛል ስለመዳኔ ላከብረው ይገባኛል ኦሆ ላመስግነው ከፍ ላድርገው ክብርን ልስጠው ኦሆ በሠማዩ መዝገብ ስሜን ስለጻፈው ደስ ይለኛል ጸድቄአለሁኝ በእርሱ ስራ ኦሆ እኖራለሁ ድንቁን ታሪኩን ሳወራ አምላክ አባት ሆነኝ በወንጌል አምኜ በደሙ ዋጋ ገዛኝ እንድኖር ልጁ ሆኜ እንግዲህ ምን ልበል ስለታላቅ ፍቅሩ ከቶ ምን ልናገር ማለዳ ማለዳ መዳኔን እያሰብኩ ከማመስገን በቀር ማለዳ ማለዳ መዳኔን እያሰብኩ ከማመስገን በቀር (2x)