አዝ፦ በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ ልብን ለይቶ የሚመረምረው እንደሰው አይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው የሚያድን ነው ደግሞ የሚራራ አቤቱ ማረኝ ላለ ወደ እርሱ ለተጠጋ ውድ ልጁ በመረቀልን በር ወደ እርሱ መግባት አለ አሄ ታላቅ ስሙ ይክበር በምክሩ ጠቢብ ፍቅሩ የላቀ በልጆቹ ላይ ግርማው የደመቀ ምሥጋና ሞላ በማደሪያው ላይ በመንጋው መልካም ማዳኑን ሲታይ አዝ፦ በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ ልብን ለይቶ የሚመረምረው እንደሰው አይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው ታናሹን ሰው ለክብር የሚያበቃው የዳዊት የሙሴ አምላክ አሄ ለትሁቱ ጠበቃ የወህኒውን መዝጊያ የሚሰብር ለባሪያዎቹ ፈራጅ የሚሆን ሞገስ ክብር አቢት እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው በመልካም ዜማ እስቲ እናምልከው ክብሩ ይታወጅ በቤቱ መድረክ የዘለዓለሙ አምላክ ይባረክ አዝ፦ በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ ልብን ለይቶ የሚመረምረው እንደሰው አይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው ተራሮችን ከላይ የሚያጠጣ ለጻድቅ ለሃጥኡ አሄ ፀሐይን የሚያወጣ ደረቁን ምድር የሚያለመልመው ለታናሹ ሰው ብርታት እህ ሞገስ የሚሰጠው ምሥጋናን ያምጡ ለእርሱ ያደሩ በመንፈሱ ኃይል እየዘመሩ የቤቱ ካህናት ምስክሮቹ ስሙን ያክብሩ ታማኝ ባሮቹ አዝ፦ በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ ልብን ለይቶ የሚመረምረው እንደሰው አይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው