Song Lyrics

ከምንጩ

Daniel Amdemichael
Yesew Iji Yelelebet
አዝ፦ ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት ለቤዛ ቀን በእርሱ ታትሜያለሁ በመንፈሱ ልደት አግኝቻለሁ ሠማያዊ ዜጋ የመንግሥቱ ተመረጥኩኘ እንድኖር በእርስቱ ፀጋ ሰጠኝ የዘለላእም ደህንነት ታማኝ ጌታ ለተደገፉበት ምሥጋናዬ ይኼው በየእለቱ ላገልግለው በደስታ በቤቱ አዝ፦ ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት አምልኮዬ ለመድሃኒዓለም ታላቅ ስሙ ይመስገን ዘለዓለም ለሚገዛው ሠማይን ምድርን አውጃለሁ ዘምራለሁ ክብሩን ለታደገኝ ለታማኝ ወዳጄ ዘምራለሁ በደስታ ፈቅጄ አወራለሁ ፍቅሩን ተዐምራቱን እርሱ ብቻ መድሃኒት መሆኑን አይገርምም ወይ በአምላክ መታሰቤ ላገለግል ለአመልከው ቀርቤ የአዲስ ኪዳን አገልጋይ በቤቱ ሎሌ አደረገኝ ጌታ በችሎቱ ኢየሱስ ይክበር ይድመቅ በሕይወቴ እርሱ አይደል ወይ ስሬ መሰረቴ ጠጥቻለሁ የዘለዓለም ውሃ ለመለመ የነፍሴ በረሃ አዝ፦ ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection