Song Lyrics

ፍጥረት የሚደገፍበት

አዝ:- ፍጥረት የሚደገፍበት እኔም ተስፋ ማደርግበት ጌታ ነው እንከን የሌለበት ልዘምር እስቲ ልቀኝለት ለሕይወት ጥያቂ ለእንቆቅልሹ ጌታ ነው ምላሽ አቻ የለሹ ሁሉንም መልካም ያደርገውና ያስገርመናል ድንቅ ይሰራና ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ይባርክና (ኦሆሆሆሆ) ሰው ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ያቆምና (ኦሆሆሆሆ) ይደግፍና እየባረኩኝ እባርክሃለሁ በሕይወትህ ድንቅን አደርጋለሁ ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እንዳልከኝ የኔ ጌታ ስንቱን አሳለፍከኝ ስንት ጊዜ አዳንከኝ ከጥፋት ልገልጽ አልችል የውለታህን ብዛት ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ ገና አመልክሃለሁ ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ እገዛልሃለሁ አዝ:- ፍጥረት የሚደገፍበት እኔም ተስፋ ማደርግበት ጌታ ነው እንከን የሌለበት ልዘምር እስቲ ልቀኝለት ለሕይወት ጥያቂ ለእንቆቅልሹ ጌታ ነው ምላሽ አቻ የለሹ ሁሉንም መልካም ያደርገውና ያስገርመናል ድንቅ ይሰራና ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ይባርክና (ኦሆሆሆሆ) ሰው ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ያቆምና (ኦሆሆሆሆ) ይደግፍና ቁሻሻውን ታሪኬን ለውጠህ ሰው አደረከኝ ኢየሱስ በእኔ ከብረህ ገና ህጻን ሳለሁ የተሸከምከኝ በጉያህ ውስጥ እስካሁን አለሁኝ አልተውህም አልጥልህም ያልከኝ ኢየሱሴ ከፍ ከፍ በልልኝ ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ ገና አመልክሃለሁ ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ እገዛልሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection