አዝ:- በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል መውጣቴ መግባቴ ከእርሱ ተጠብቆ ባለፍኩበት መንገድ ጌታ ለእኔ ተተንቅቆ በምህረቱ ታድጓታል ነፍሴን ከእሳት ነጥቆ የእርሱን ደግነት ለሰው እነግራለው አያሳፍርም ሁሌ ታማኝ ነው በሥም የሚያውቀኝ የሆነኝ ጥላ ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ከለላ አዝ:- በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል ትንፋሼን መንገዴን በእጁ ለያዘው የሰማዩን ፍቅር ሰላም ውስጤ ላፈሰሰው በማዳኑ ደስ እያለኝ አመሰግናለሁ ታሪክም የለኝ ታሪኬ እርሱ ነው ከልጅነቴ እጄን የያዘው ምስክሩ ነኝ ዘለዓለም ይንገሥ መልካም እረኛ ስሙ ኢየሱስ አዝ:- በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል