Song Lyrics

አምነዋለው

አዝ:- አምነዋለው ኦሆሆ ሁሉ በእርሱ እንዲሆን አውቃለሁ የኢየሱስ ቃል አለኝ አሃሃ ነግሮኛል እንደማይጥለኝ እህህ ስሙን እየጠራሁ ለቀድሞ የታመንኩበት ጊዜ አይለውጠውም ለዛሬም ልቤን ጣልኩበት የሕይወት ጓደኛ ነው ጌታ ኢየሱስ ለታመኑበት እስከሽምግልና ይሸከማል ወረት የሌበት ይሸከማል (3x) ወረት የለበት (2x) ድንቅ ሰላም አለኝ ሁልጊዜ የማይጠፋ በልቤ የታተመ ከቶ ማይደፈርስ በወጀብ በማዕበል ውስጥ ከሰማይ የሆነ የሰጠኝ የእግዚአብሔር ልጅ (2x) ቆማለሁ ቃሉ ነግሮኛል አልሰጋም ፍቅር ይዞኛል አያልቅም የእርሱ ቸርነት ጥላ ነው ለታመኑበት ማረፊያ ነው መጠጊያ ነው ልቡን ለጣለበት (2x) አዝ:- አምነዋለው ኦሆሆ ሁሉ በእርሱ እንዲሆን አውቃለሁ የኢየሱስ ቃል አለኝ አሃሃ ነግሮኛል እንደማይጥለኝ እህህ ስሙን እየጠራሁ ለቀድሞ የታመንኩበት ጊዜ አይለውጠውም ለዛሬም ልቤን ጣልኩበት የሕይወት ጓደኛ ነው ጌታ ኢየሱስ ለታመኑበት እስከሽምግልና ይሸከማል ወረት የሌበት ይሸከማል (3x) ወረት የለበት (2x) ምህረቱ ይገርመኛል የአምላኬ ፍቅር ግሩም ነው ምህረቱ ይደንቀኛል የጌታዬ ፍቅር ግሩም ነው ምህረቱ ይገርመኛል የኢየሱስ ፍቅር ግሩም ነው ምህረቱ ይደንቀኛል የአምላኬ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የአምላኬ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የኢየሱስ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የጌታ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የአባቴ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የኢየሱስ ፍቅር ግሩም ነው ኦ ግሩም ግሩም የአባቴ ፍቅር ግሩም ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection