Song Lyrics

ምህረቱን አይቼ ነው

የጌታን ቸርነት ምህረቱን ሳስበው መውጣቴ መግባቴ መኖሬ በእርሱ ነው ለእኔ የበዛው ፍቅር እጅግ ይገርመኛል ሁሌ ሳታቋርጥ አመስግን ይለኛል እጆቼን ወደ ጌታ ወደ ኢየሱስ ዘርግቼ አመሰግነዋለሁ ስለተዋቡት ቀኖቼ ኢየሱስ ሕያው አለት የኔ ጽኑ መሰረት ምሥጋና ይብዛህ እንጂ ምሥጋና አይነስበት አዝ:- ምህረቱን አይቼ ነው ፍቅሩን ቀምሼ ነው ዛሬ ደስ ብሎኝ በፊቱ ቆሜ ምዘምረው (2x) በአባትነት ፍቅሩ ሁሌ እየመከረኝ እግሬ ሲንሸራተት ይዞ እየደገፈኝ በጸጋው ከልሎ እዚህ አድርሶኛል እንዳመሰግነው ውስጤ ግድ ይለኛል ልዘምር ለጌታዬ እርሱ ምሥጋናዬ ነው እግሬን እመሰናከል ነፍሴ ከሞት ላዳነው ልቅረብ በፊቱ ልስገድ ጌታ ኢየሱስ ወዶኛል ሁልጊዜ ጠዋት ማታ ሳመልከው ደስ ይለኛል አዝ:- ምህረቱን አይቼ ነው ፍቅሩን ቀምሼ ነው ዛሬ ደስ ብሎኝ በፊቱ ቆሜ ምዘምረው (2x) ተአምራቱን ያየ ፍቅር የበዛለት ድንቁ ጌታ ኢየሱስ ሞገስ የሆነለት ሳይቆጥብ ይናገር ያውራ የእርሱን ስራ ተአምር እንደሚያድርግ ድንቅን እንደሚሰራ ይናገር የቀመሰ ፍቅሩን መልካምነቱን የሚያድን የሚታደግ ሩህሩህ አባት መሆኑን አምላክ ነው የሚያስመካ እረዳት ድንቅ ሰሪ ዘመኑ ቁጥር የለው ጌታ ዘለዓለም ነዋሪ አዝ:- ምህረቱን አይቼ ነው ፍቅሩን ቀምሼ ነው ዛሬ ደስ ብሎኝ በፊቱ ቆሜ ምዘምረው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection