Song Lyrics

በአንተ ደስ ይለኛል

አዝ:- አሁንማ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል ምን እላለሁ ስምክን ከማክበር በቀር ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (2x) በዓለም ላይ ከሚታየው ከአልማዝ ከወርቅ ከዕንቁ የአንተ ፍቅር ይበልጣል አባት ነህ ለተጠቁ ምስክር ነኝ ለዚህ እኔ ማዳንህን አይቻለሁ ያባትነት ፍቅርህን ምህረትህን እዘምራለሁ ተመስገን እያልኩ ላክብር ስምህን በእርግጥ ስላየሁ ጌትነትህን በአማረ ዜማ ቅኔ ውዳሴ ልዑል ከፍ በል ያክብርህ ነፍሴ አዝ:- አሁንማ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል ምን እላለሁ ስምክን ከማክበር በቀር ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (2x) ማረፊያ ለምስኪኑ ማጠጊያ ለደሃው ሰው ይህንን አይቻለሁ እንባውን ስታብሰው ደግ ነህ እግዚአብሔር መልካም ግሩም በምክርህ ምህረትህ አይለካም ወደር የለው ለፍቅርህ አሉ ብዙዎች የታደጋቸው ስምህን የሚጠሩ በምሥጋናቸው እያደነቁ ግሩም ስምህን ይዘምራሉ ጌትነትህን አዝ:- አሁንማ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል ምን እላለሁ ስምክን ከማክበር በቀር ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection