አዝ:- ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ መልካም አምላክ ነው ሰላምን ይሿታል በወርቅ በብር ሊያገኟት በዓልማዝ በዕንቁ አትመጣም ምን ያህል ቢያፈሱላት ከእግዚአብሔር የታረቀ እርሱ ነው የዘየደ በአምላክ ሰላም ይጠግባል በመንገዱ የሄደ (2x) በፈቃዱ የሄደ (2x) አዝ:- ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ መልካም አምላክ ነው ሆድ በእንጀራ ቢሞላ ገላም ምርጡን ቢለብስ የነፍስ ጐዶሎ አይሞላም ሰው ሁሉን ቢያግበሰብስ ሰማያዊው ደስታ አምላክ ከላይ የላከው ሰላም ማለት ኢየሱስ ነው ተሰፍሮ የማይለካው (2x) ሰው ዓለምን አትርፎ ውድ ነፍሱን ቢያዶላት ከቶ ምን ይጠቅመዋል መጨረሻው ነው ጥፋት ብሩክ ትሁን ያቺ ቀን ወንጌል የሰማሁባት በክርስቶስ መስቀል ስራ ከአምላክ ጋር የታረቅኩባት (2x) ወንጌል የሰማሁባት አሄ ሰላም ያገኘሁባት አዝ:- ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ መልካም አምላክ ነው