Song Lyrics

ኢየሱስ

ያ የጥንቱ ፍቅራችን መሃላችን የታለ ኀጢአታችን በዝቶ ጥላቻን አበቀለ ከአንተ ያልተቀበልነው ያልሰጠኀን ምን አለ ሁሉም ተረስቶ ዛሬ ትዕቢታችን ከፍ አለ አዝ:- ኢየሱስ (2x) በማስተዋል ሙላን በማስተዋል (2x) ኀጢአት ከንቱ ነው አይሆንም ለማጥ ሞትን ይወልዳል ለሕይወት ጥፋት ደሙ ያላጠበው ያልተመለሰ እናስብ እንጂ ከየት ደረሰ ምክንያት አንደርድር ለድካማችን ከሞት ያድናል መመለሳችን ኑሯችን ከንቱ ከእውነት የሚጣረስ ንሰሃ እንግባ ሳናለባብስ ቦታ አጥቶ ቅድስና ኀጢአት ተሞልቷል ቤቱ ሁሉም አንተን አልፈራም ይስታል በአንደበቱ የጥበብ መጄሪያው አንተን መፍራቱ ጠፍቶ ሁሉ እንዳሻው ይሄዳል ቤቱ በአመጽ ትሞልቶ አዝ:- ኢየሱስ (2x) በማስተዋል ሙላን በማስተዋል (2x) ከየት ተማርነው ወንድምን መጥላት ከነብያት ነው ወይንስ ከሓዋርያት የቀደሙትን የምናውቃቸው በመልካም ፍቅር በጸኦታቸው ለእውነት እንኑር ከቶ አንገበዝ ደሙ ያነጻናል ትሎ እንመለስ የሰማይ ጥበበ የላይኛይቱን ከአምላክ እንለምን ይሰማል ሁሉን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection