Song Lyrics

አምላኬ ነህ

Daniel Amdemichael
Mogninet Hono Ayidelem
እኔማ ምን ልበል ስንቱን አወራለሁ የቱንስ አውርቼ የቱን እተዋለሁ ያደረገልኝን ብቆጥር በየተራ ከአዕምሮዬ በላይ ሆነ የእርሱ ሥራ እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ ከአዕምሮዬ በላይ ነው የእርሱ ሥራ (2x) ክብር የእግዚአብሔር ነው ክብር የኢየሱስ ነው (2x) ተመስገን የምለው ካሳ ሆኖ አይደለም የጌታን ውለታ የሚክሰው የለም ክበርም የምለው ስለሚገባው ነው ለውለታው ምላሽ ሊሰጥ የሚችል ማነው እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ ከአዕምሮዬ በላይ ነው የእርሱ ሥራ (2x) አዝ፦ አምላኬ ነህ ጌታዬ/ኢየሱሴ ወዳጄ እንከን የሌለህ ፍቅርህ ለእኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ (2x) ስለዚህ (2x) በፍፁም ልቤ ጌታዬ ወድሃለሁ ዘመኔን (2x) እያከበርኩህ ለመኖር ወስኛለሁ (2x) ከእርሱ የሆነውን ለእርሱ አቀርባለሁ እኔማ ምን አለኝ ምን እሰጠዋለሁ እንዲሁ በፀጋው ፊቱ አቁሞኛል ስለፈቀደልኝ አመስግን ብሎኛል ስለፈቀደልኝ አሃሃ አመስግን ብሎኛል አሃሃ ስለፈቀደልኝ ኦሆሆ አክብረኛል ብሎኛል አሃሃ አዝ፦ አምላኬ ነህ ጌታዬ/ኢየሱሴ ወዳጄ እንከን የሌለህ ፍቅርህ ለእኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ (2x) ስለዚህ (2x) በፍፁም ልቤ ጌታዬ ወድሃለሁ ዘመኔን (2x) እያከበርኩህ ለመኖር ወስኛለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection