አዝ፦ ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል የድሃ አደግ ወዳጅ የምስኪን ጓደኛ ማን እንደ ኢየሱሴ ታማኝ ሚስጥረኛ መድኃኒቴ እርሱ ነው ሁሌ አመልከዋለሁ ምሥጋናም ክብርም ዝማሬም ለእርሱ ነው (6x) አዝ፦ ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል ኃጥያተኛ ብሎ ሁሉም ተፀይፏት ያለርህራሄ በድንጋይ ሊወግሯት እንዳትሞት የሚፈልግ ተገኘ የሚወዳት ጥበብን ተናግሮ ከጨካኙ አዳናት አትሞቺም አላት(5x) አዝ፦ ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል የአንዲቷ ነፍስ ጌታን በጣም ግድ ብሎት በሰማሪያ መንገድ አለፈ ሊያድናት የነፍሷን ጥያቄ የውስጧን ፈታላት የሕይወትን ውኃ አፍለቀለቀላት አትጠሚም አላት(5x) አዝ፦ ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ያስገርመኛል አቤቱ ጌታዬ ሁሌ አከብርሃለሁ ፍቅርህን እያሰብኩ እገዛልሃለሁ ምሥጋና ይገባሃል ንገሥ ለዘለዓለም በሰማይ በምድር ኧረ እንዳንተ የለም (6x)